ሀጅ አላህ በአገልጋዮቹ ላይ የደነገገውና ከእስላም ማእዘናት አንዱ የሆነ ማእዘን ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል ፡- ‹‹ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን፣ በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፤ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡›› [ኣል-ኢምራን:97]
በዚህ መተግበሪያ ውስጥ የተካተቱ ርዕሶች
- ሐጅና ዑምራን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች
- ሐጅን የሚመለከት የትውውቅ መቅድም
- የዑምራ ማእዘናት ዋጅቦችና ሱናዎች
- የሐጅ ማእዘናት ዋጅቦችና ሱናዎች
- የመዲና ጉብኝት የመዲና ትሩፋትና የላቀ ደረጃዋ
- ፍድያ (ቤዛ) እና ሀድይ
- ሚቃቶች
- ኡድሕይ’ያ
- የሐጅና ዑምራ አፈጻጸም
- ኑሱክ እና ተልቢያ
- እሕራም እና ሌሎችም።