እግዚአብሔር ያከበራችሁ መላእክትም ጻድቃንም ምስጋናዋን የማይቻላቸው የማይቻላቸው እመቤታችንን ተአመር ለመስማት አይነ ያብራ ያብራ ላችሁ። ልመናዋ በረከትዋ ከሀብተውልድ ጋር ለዘላለሙ ይኑር። ከተአምር አስቀድሞ ይነበብ ሕዝብም እዝነ ልቦናቸውን ከፍትው ይስሙ። በእብራይስጥ ማሪሃም የምትባል የመቤታችንን ክብርዋን ልእልናዋን ምስጋናዋንም በልቦናችሁ አሳድሩት። ማርያም ማለት መንግስተ ሰማይ መርታ የምታገባ ማለት ነው።