30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ

5,0
364 ta sharh
100 ming+
Yuklanmalar
Yoshga oid cheklov
3+
Skrinshot
Skrinshot
Skrinshot
Skrinshot
Skrinshot
Skrinshot
Skrinshot

Bu ilova haqida

በአላህ ስም በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው
የአላህ ሰላትና ሰላም ከፍጡራን ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነብያችን (ﷺ) ላይ ይውረድ።

ይህ አፕ ምርጥ የሆኑትን የነብያችን ﷺ ባልደረቦች ታሪክ በአጭሩ አካቶ ይዟል።
ሶሀቦች ቁርአንን የህይወታቸው ብርሀን አድርገው ይዘውታል። የኢስላምን መርሆችና አስተምህሮቶች ወደ ህይወት ለውጠዋል። በስነ ምግባር ምጥቀት ስፋትና በአላማ ፅናት እንዲሁም በመልካም ስብዕና ከፍተኛ ደረጃ ለመድረስ በቅተዋል ።
ነብዩም(ﷺ) እንዲህ ሲሉ አወድሰዋቸዋል
"ከሁሉም ምርጡ ትውልድ እኔ የምገኝበት ትውልድ ነው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው …"
ታላቁ ሶሀባ ዐብደላህ ዒብነ መስዑድ የሶሀቦችን ገድል በዘከሩበት ንግግራቸው እንዲህ ይሉናል፦
"አረአያ ሊሆን የሚችል ስብዕና የሚሻ ካለ የመልዕክተኛው ባልደረቦች ብቻ ናቸው አርአያ ሊሆኑ የሚችሉት እናም የሶሀባ ትውልድ አባላት። ምክንያቲም እነሱ ከማንም በላቀ ሁኔታ የጠለቀ ዕውቀት ባለሀብቶች ነበሩና። ቀጥተኛውን ጎዳና መርተዋል። አላህ ለመልእክተኛው ባልደረባነት አጭቷቸዋል ። የዚህን ዲን ታላቅ አደራ ተሸክመዋል። ማንነታቸውን እወቁ ፣ፈለጋቸውንም ተከተሉ ፣ ቀጥተኛውን የህይወት መንገድ የተከተሉ ሰወች ነበሩና።
በየትኛውም ቦታና ጊዜ የምንገኝ ሙስሊሞች የዚያ ድንቅ ትውልድ ፤የዚያ ቁርአናዊ ማህበረሰብ አባላት አርአያነት እንደሚያስፈልገን ግልፅ ነው።ከሶሀባ ትውልድ ታሪክ በጣም ብዙ እንማራለን።ከምርጥ ስብእናቸው የጠራ ምንጭ እንጎነጫለን ። በህይወት ውስጥ ያደረጉት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ለህይወት ጉዟችን ብርሀን ነው ። የማንነታችን መለያ ነው…"።ከቀደምቶች ታሪክ እራሳችንን እንድናስተምር ይህ የሶሀበች ታሪክ የሚለው አፕ አስተማሪ ይሆናል ብለን እናስባለን።
በዚህ አፕ ታሪካቸው ያልተጠቀሱ ብዙ ሶሀቦች አሉ፤ በአላህ ፍቃድ በየግዜው የሌሎችም ሶሀቦች ታሪኮችን አካተን አፑን በየግዜው እናድሰዋለን፣ ከእርሶ የሚጠበቀው ይህን አፕ በየግዜው ማዘመን/Update ማድረግ ነው።

ከአጅሩ ተቋዳሽ ይሆኑ ዘንድ አንብበው ለሌሎችም ያጋሩ።

ይህ ስራችን የተከበረው የአላህን ፊት ተፈልጎበት የተሰራ እንዲሆን እንዲሁም ታሪኩን ከተለያዩ ምንጮች ላሰባሰቡ ፀሐፊዋች ለኛም በዚህ ስራ ለተባበሩንም በሞት ለተለዩንም ይህንን ስራ ለሚያሰራጩትም ከሁላችንም  ይቀበለን ዘንድ አላህን እማፀነዋለሁ።

በአላህ ፍቃድ ሌሎች ጠቃሚ አፖችን አዘጋጅተን በቀጣይ እናደርሳችኃለን።
________________
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል - ከናንተ ውስጥ መጥፎን ነገር ያየ በእጁ ይቀይር ካልቻለ በምላሱ ካልቻለ ደግሞ በልቡ ይጥላ ይህ ግን (በልብ ብቻ መጥላት) ደካማ ኢማን ነው" (ሙስሊም ዘግበውታል)
ወንድም እህቶቼ ታሪኩን በምታነቡበት ግዜ ከቁርአን ከሀዲስ የተጨመረ ወይም የተቀነሰ ነገር ካገኛችሁ በአድራሻዬ አድርሱኝ።
ስህተቴን ላረመኝ ሰው አላህ ይዘንለት።

አላህ ሆይ!ጠቃሚ እውቀትን ከተግባር ጋር ወፍቀን መጨረሻችንንም አሳምርልን አሚን! ከተሳሰትኩ ከነፍስያዬና ከሸይጧን ሲሆን ሐቅን ከገጠምኩኝ ከአላህﷻ ነው።

የአፑ አዘጋጅ አብዱራሂም ማህሙድ

※ከዚህ በፊት ያዘጋጀነውን የነብያት ታሪክ አፕ በሚከተለው ሊንክ መጫን ይችላሉ፦
/store/apps/details?id=qissa.anbia.hudasoft
Oxirgi yangilanish
31-okt, 2022

Maʼlumotlar xavfsizligi

Xavfsizlik — dastur ishlab chiquvchilar maʼlumotlaringizni qanday jamlashi va ulashishini tushunishdan boshlanadi. Maʼlumotlar maxfiyligi va xavfsizlik amaliyotlari ilovadan foydalanish, hudud va yoshga qarab farq qilishi mumkin. Bu axborot dastur ishlab chiquvchi tomonidan taqdim etilgan va keyinchalik yangilanishi mumkin.
Tashqi hamkorlarga hech qanday axborot ulashilmagan
Dastur ishlab chiquvchilar axborot ulashilishini qanday aytishi haqida batafsil
Hech qanday maʼlumot jamlanmagan
Dastur ishlab chiquvchilar axborot jamlanishini qanday aytishi haqida batafsil

Reytinglar va sharhlar

5,0
355 ta sharh

Nima yangiliklar

30+ Story of Sohabas