ስለ ኢስላማዊ ስርአቶች በስፋት የሚዳስሰውን አል ወጂዝ የተሰኘውን ኪታብ በድምጽ እና በጽሁፍ የያዘ መተግበሪያ ሲሆን መተግበሪያው ለመጠቀም ምቹ እና ቀላል እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ ነው።
* የኪታቡን pdf እና ድምጽ አጣምሮ የያዘ
* ኪታቡ ውስጥ ላይ ባለው ክፍፍል መሰረት በርእሶች ከፋፍሎ የያዘ
* በምንቀራበት ሰአት እያንዳንዱ ክፍል ውስጥ ማስታዎሻ መያዝ የሚያስችለን
* በሌላ ጊዜ እንደመነሻነት የምንፈልግበት ቦታ ላይ ምልክት ማድረግ የሚያስችለንአፕሊኬሽንነው።
ኪታቡበውስጡ
* ከ አላህ ጋር ሊኖረን ስለገባ ስርአት
* ከነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ጋር ስለኖረን የሚገባ ስርአት
* ከቁርአን ጋር ሊኖረን ስለሚገባ ስርአት
* ከነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሱናዎች ጋር ሊኖረን ስለሚገባ ስርአት
* ከነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች ጋር ሊኖረን ስለሚገባ ስርአት
* የእውቀት እና ከእውቀት ባለቤቶች ጋር ሊኖረን ስለሚገባ ስርአት
* ወደ አላህ መንገድ የመጣራት ስርአት
* በመልካም የማዘዝ እና ከመጥፎ የመከልከል ስርአት
* ከወላጆቻችን ጋር ሊኖረን የሚገባ ስርአት
* የትዳር ህይዎት ስርአት
* የወንድማማችነት ፣ የጓደኝነት እና የወዳጅነት ስርአት ወዘተ
እነዚህን እና ሌሎችንም ወሳኝ ትምህርቶችን በዚህ ክፍል ውስጥ የያዘ ሲሆን ሁሉም ሙስሊም ሊማረው የሚገባ ወሳኝ ኪታብ ነው። መተግበሪያውን ለመጠቀም ምንም አይነት የኢንተርኔት ኮኔክሽን አይጠይቅም።
መልካምትምህርት